የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በግራ ዘመም እና መሠረተ-ጎሳ በሆኑ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰቦች ዘንድ በጠላትነት እንደምትፈረጅ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በዚህ ረገድ የሕወሐት የ40 ዓመት ፖለቲካ እና በኦነግ እና ከዚያም በኋላ በተነሡ የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ያለው አመለካከት ተጠቃሽ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የፈረጁበትን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው ብናቆየው እና በኦሮሞ ልሒቃን አካባቢ የሚጠቀሰውን አንድ መጽሐፍ (ራእየ ማርያምን) ብቻ ብናነሣ፣ ጥላቻው መሠረት የሌለው ይልቁንም በግልሰቦች ስሕተት እና ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህም በራእየ ማርያም ላይ በግእዝ መጻሕፍት ላይ ጥናት በሚያደርጉት በዶ/ር አምሳሉ ተፈራ «የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር» በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን መሠረታዊ ጥናት እንድታነቡ እንጋብዛለን። ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ሊንክ («የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር») ይጫኑ።